ስንፈተ ወሲብ ምንድነው?

1; ስንፈተ ወሲብ(sexual dysfunction) ማለት በሁለቱም ፅዎታዎች በኩል በተለያየ ምክንያቶች አግባባዊ(የሚያረካ) የግብረስጋ ግንኙነት አለመፈፀም ወይም አለመርካት ማለት ነው።

2; የሰንፈተ ወሲብ አይነቶች

A;የወሲብ ፍላጎት ማጣት(sexual desire disorder)

B;የብልት አለመነሳሳት/ አለመቆም(erectile dysfunction)

C;የዘር ፈሳሽ ቶሎ መፍሰስ(premature ejaculation)

D;በሴቶች ላይ የወሲብ ፍላጎት መቀዝቀዝ/ አለመኖር(frigidity)

E;በወሲብ ግዜ አለመርካት(orgasm disorders)

F;በወሲብ ግዜ የሚፈጠሩ የህመም

ስሜቶች(sexual pain disorders)

3;ምልክቶቹ

*ለግብረስጋ ግንኙነት ስሜት ማጣት

*የብልት አለመነሳሳት/ አለመቆም

* ቶሎ የዘር ፈሳሽ መፍሰስ እና ብልት መልፈስፈስ

* ለግንኙነት የሚሆን በቂ ፈሳሽ አለማመንጨት( ለሴቶች)

*የእርካታ መጨረሻ ላይ አለመድረስ

*በግንኙነት ወቅት ጫን ያለ ህመም መሰማት

4; መንስኤዎቹ

የችግሩ መንስኤዎች አካላዊ እና ስነልቦናዊ ብለን በ ሁለት ዋና ዋና ከፍለን እንመለከታቸዋለን

አካላዊ መንስኤ ማለት= ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች ወይም estrogen ሆርሞን መቀነስ( በሴቶች) እና የ testosterone ሆርሞን መቀነስ ( በሁለቱም ፅዎታ) ሲሆን

* ብልት እንዲቆም የሚያደርጉ ነርቮች ባለመስራታቸው

* በብልት ላይ የተለያዩ አደጋዎች ሲደርሱ እና ደምስሮች ሲጎዱ

* በቀዶ ጥገና የፅዎታ ለውጥ ሲደረግ

*የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ስኩዋር፣የልብ ህመም፣የኩላሊት ህመም፣የደምስር ችግሮች፣ግፊት፣ እና የነርቭ ህመም የመሳሰሉት ሲኖሩ እና

*ለሌሎች በሽታዎች መፈወሻ የሚወሰዱ መድሀኒቶች ችግሩን ሊያባብሱ ወይም ሊያስከትሉ ይችላሉ ለምሳሌ_የጨጉዋራ መድሀኒት(cimetidine)_ የደም ግፊት(methyldopa)_ ለሽንት ማሸኛ(furosemide)_ለ አይምሮ ህመሞች የሚሰጡ (phenytoin) እና ሌሎችም የካንሰር መድሀኒቶች ችግሩን ሊያመጡ ይዘችላሉ

ስነ ልቦናዊ ማለት= ብዙን ግዜ በወቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ለአብዛኞቹ የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ለምሳሌ እንደ የዘር ፈሳሽ ቶሎ መፍሰስ እና በሴቶች ላይ የወሲብ ፍላጎት መቀዝቀዝ ዋና መንስኤ ነው።

* ድብርት፣ጭንቀት፣ጫና እና ውጥረት፣መደፈር እና ከማያፈቅሩት ሰው ጋር ወሲብ መፈፀም

* በአንድ ወቅት ችግሩ አጋጥሞት/ ሟት ከነበረ ሁልግዜ ችግሩ አለብኝ ብሎ መጨነቅ

*የወሲብ ተጉዋዳኝ ስድብ እና ዘለፋ ለምሳሌ ሴቱዋ አልረካሁም አትችልም ችግር አለብህ ማለት ነገሩን ሊያባብስ ይችላል

* ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ አብዝቶ አልኮል መጠጣት፣ሲጋራ ማጨስ፣አሺሽ እና የመሳሰሉት ነገሮች ችግሩን በበለጠ የሚያባብሱ መሆናቸውን እየገለፅን የአንድን ነገር መንስኤ ማወቅ ለመፍትሄው አቅጣጫ ነውና ይታሰብበት እንላለን!

5; አማራጭ የህክምና መፍትሄዎች

የስንፈተ ወሲብ ህክምና እንደ መንስኤው አይነት የተለያዩ ናቸው ችግሩ የተከሰተው በስነ ልቦናዊ ችግር ከሆነ ከተቻለ እራስን በማረጋጋት መፍትሄ ለማግኝት መሞከር ይገባል ለምሳሌ የዘር ፈሳሼ ቶሎ ይፈሳል ብሎ ከመጨነቅ እንደዚ አይነቱ ችግር በስነልቦና የሚመጣ መሆኑን ተገንዝቦ ከወሲብ ጉዋደኛ ጋር በመመካከር ችግሩን ለመቅረፍ መጣር ይገባል ካልተቻለ ግን ወደ ስነልቦና ባለሞያ በመሄድ አስፈላጊውን መፍትሄ ማግኝት ይቻላል እንደ ሲጋራ፣ጫት ያሉትን ነገሮች ፈፅሞ በማቆም ስነልቦናዊ የወሲብ ችግርን መከላከል ይቻላል።

በአካለዊ መንስኤ ማለትም በውስጥ ህመም ምክንያት የመጣ ከሆነ ግን ወደ ሀኪም ጎራ በማለት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ መፍትሄ ማግኝት የሚቻል ሲሆን በመጠኑም ቢሆን ስለ ህክምናው እንጠቁማቹ

*በአጠቃላይ የስንፈተ ወሲብ ችግር ከመድሀኒት እስከ ቀዶ ህክምና የሚዘልቅ የህክምና መፍትሄ ያለው ችግርነው

*አትክልት እና ፍራፍሬ መመገብ

* ከልክ ያለፈ ውፍረት መቀነስ

*የምክር አገልግሎት ማግኝት

*ወንዱ ላይ ችግር ካለ ሴትዋም ተጎጂ ናትና መልካም ነገር በመናገር የፍቅረኛዋን ስነ ልቦና ማከም

* ከመድሀኒት የጎንዮሽ ጉዳት ጋር ተያይዞ የመጣ ከሆነ ሀኪሞን በማማከር መድሀኒቱን ማቆም ወይም መቀየር

* የሆርሞን እጥረት ላለባቸው የሆርሞን መተኪያ ህክምና(testosterone replacement)

* በቀዶ ህክምና የተፈጠረውን ችግር ማስተካከል

* በሀኪም የሚታዘዙ መድሀኒቶ ለምሳሌ sildenafil( viagra or cupid) tadalafil vardenafil avanafil የደም ዝውውርን በመጨመር ለችግሩ መፍትሄ ይሆናሉ

*በግንኙነት ግዜ የሚፈጠር ህመምን ለማስቀረት ለዚሁ በተዘጋጁ ማለስለሻዎችን መጠቀም

* የነርቭ ችግር ካለ በነርቭ ሀኪም መታከም

ወድ አንባቢያን ከላይ የተጠቀሱትን መድሀኒቶች ያለ ሀኪም ትዛዝ መውሰድ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል እና ጠንቀቅ!!!

Click Here to Learn More